
ዋና አስተዳዳሪው ይህን ያሉት የዞኑ ጤና መምሪያ የወባ በሽታ ወረርሽኝ ለመከላከልና ለመቆጣጠር ያለመ የንቅናቄ መድረክ በወራቤ ከተማ ባካሄደበት ወቅት ነው።
ወራቤ ጥቅምት 5/2017 ዓ.ም ፣ሰልጤ ዞን ኮሙኒኬሽንመምሪያው በንቅናቄ መድረኩ ላይ የወባ በሽታ ስርጭትን በመከላከልና በመቆጣጠር ዙሪያ ከባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት በማድረግ በሰፊው መክሯል። በንቅናቄ መድረኩ ላይ ንግግር ያደረጉት የስልጤ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዘይኔ ቢልካ እንዳሉት የወባ በሽታ አርሶአደሩን ብሎም ህብረተሰቡን ከዕለተ ተዕለት ስራው የሚነጥል ነው። ይህም ወረርሽኙን ከወዲሁ መከላከልና መቆጣጠር ካልተቻለ በሀገር ብሎም በዞን ደረጃ በማህበራዊ፣ ኢኮኖሚና ፖለቲካ የሚያሳድረው ተፅዕኖ ቀላል የሚባል አይደለም ብለዋል።
Read More